SOZO Acoustic Band - Rabirabay

የስሙ ጠረን መአዛ ሽቶ
ለወጠኝ እኔን ውስጤ ገብቶ
ትንፋሹ ለነብስ መዳኒት ነው
አዎ
ሲያዩት ከሩቅ ይማርካል
ሲጠሩት ቀርቦ ልብ ያረካል
ያውዳል እሱን ለቀመሰው
አዎ

ስሙ መድሃኒት ነው ደግሞም ሽቶ
ሕይወት ነብስ ይዘራል ከልብ ገብቶ
አንደ ዘይት ፈሶ ለጋ ያደርጋል
የሞተን እስትንፋስ ደግሞ ያስነሳል

እንደ ካህን ዘይት ሽታ
የሱ ጠረን ያርቃል በሽታን
ልብን ይጠግናል
ዐጥንትንም አልፎ
እስከ ነብስም ደርሶ
አቤት፦ ሲፈውስ ሲጠግን ሲያጽናና
ይለያል ከሌላው

ስሙ መድሃኒት ነው ደግሞም ሽቶ
ሕይወት ነብስ ይዘራል ከልብ ገብቶ
ሊቀ ካህን ነው ይሄ ጌታ
ህይወትን ሚሰጥ ለዛ ሽታ
ልዩ ናዝራዊ ስሙ ነው ጌታ
የህይወት ሽታ

ሊቀ ካህን ነው ይሄ ጌታ
ህይወትን ሚሰጥ ለዛ ሽታ
ልዩ ናዝራዊ ስሙ ነው ጌታ

ዕንኮይና ከርቤ
ስለው ደስ ይለኛል ከልቤ
እጅግ የሚናፈቅ
እንደ ዘይት ፈሶ
ድርቀትን አርሶ
እሱ እርጅናን ዘወትር የሚያድስ
ስብራት ሚፈውስ

ስሙ መድሃኒት ነው ደግሞም ሽቶ
ሕይወት ነብስ ይዘራል ከልብ ገብቶ
ሊቀ ካህን ነው ይሄ ጌታ
ህይወትን ሚሰጥ ለዛ ሽታ
ልዩ ናዝራዊ ስሙ ነው ጌታ

እርሱ
አዎ እርሱ
ያለ የነበረ ነው እርሱ
አዎ እርሱ
ያለ የነበረ ነው እርሱ
መዓዛው መድሃኒት ነው
ስሙ
ደህንነት ፈውስ ያለው
ስሙ
ማይሰለች ጠረን ናርዶስ
ስሙ
እደዚህ ነው ስሙ ኢየሱስ
ስሙ

ስሙ እንደ ዘቢብ
የማይጠገብ
ልዩ እንደ ሮማን
መሆኑ ገባን

መዓዛው መድሃኒት ነው
ኢየሱስ
ደህንነት ፈውስ ያለው
ኢየሱስ
ማይሰለች ጠረን ናርዶስ
ኢየሱስ
እደዚህ ነው ስሙ ኢየሱስ

ስሙ እንደ ዘቢብ
የማይጠገብ
ልዩ እንደ ሮማን
መሆኑ ገባን

አዎ ያለነው እሱ
ያለ የነበረ ነው እሱ
አዎ ያለነው እሱ
ያለ የነበረ ነው እሱ

ትንፋሹ ለሕይወት
ኢየሱስ
መዓዛ የሚሞላ አልባስጥሮስ ነው
እሱ
ጠረንን የሚቀይር
ኢየሱስ
እጅግ የሚያርስ ለዛ ያለው
ረቢ ረቢ
ትንሣኤን ይሰጣል
ረቢ ረቢ ረቢራባይ
መንፈስን ያውዳል
ረቢ ረቢራባይ
እንደ ዘይት ጠል አርሶ
ረቢረቢረቢራባይ
ያለማቋረጥ ይወርዳል

ረቢ ረቢ ረቢራባይ
ረቢ ረቢ
ረቢ ረቢራባይ

ረቢ ረቢራባይ
ረቢ ረቢራባይ
ረቢራባይ

Written by:
Matiyas Berza

Publisher:
Lyrics © O/B/O DistroKid

Lyrics powered by Lyric Find

SOZO Acoustic Band

View Profile